[go: up one dir, main page]

Jump to content

ኣስያ ቢንት መህዙም

ከውክፔዲያ

| ስም = አስያ | = የአንሽየንት ዘመን ንግስት | ሰእል= http://www.touregypt.net/images/touregypt/ramessesIIgirls7.jpg | የሚገልጸዉ = ንግስት አስያ የ ራምሰስ ሁለተኛ ሚስት ተብል በዛን ዘመን ከተሳሉት ሰሎች በጥናት የተገኘ | ሙሉ ስምዋ = አስያ ቢንት መህዙም | የተለያዩ ስምዎችዋ = የታላቁ ንጉስ ሚስት፣ ባለ ሁለት መሬት ሴት፣የታችኛዋን እና የላይኛዋ ኢጅብት ንግስት. | የተወለደችበት ቀን = ያልታወቀ | የተወለደችበት ቦታ = ግብጽ | የሞተችበት ቀን = 1199 B.C.E | የሞተችበት ቦታ = ግብጽ | የቀብርዋ ቀን = 1198 B.C.E | ባልዋ = ፊርአዉን ራምሰስ ሁለተኛ | እምነት = በፊት ጣኦት አምላኪ ቡሃላ ግን እስልምናን ተቀብላ ነዉ የሞተች

አስያ ከሀዲስ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ኣንድ ቀን ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.አ.ወ) መሬት ላይ አራት መስመሮችን አሰመሩ ከዛም ለባልደረቦቻቸው አነዚህ መስመሮች ስለምን ይመስላቹሃል ሲሉ ጠየቁ ሱሃቦቹም አላህ እና መልእክተኛው ያውቃሉ ሲሉ መለሱላቸዉ። ነብዩ (ሰ.አ.ወ)እንዲህ ሲሉ ቀጠሉ እነዚህ በምድር ላይ መላኢካ ያናገራቸዉ ምርጥ ሴቶች ኣስያ ቢንት መህዙም የፊርአዉን ሚስት፤የኢምራን ልጅ መርየም የእየሱስ (አ.ሰ) እናት ኸድጃ ቢንት ኹወይሊድ የነብዩ ሙሃመድ(ሰ.አ.ወ) የመጀመርያ ሚስት እና ፋጡማ ቢንት ሙሃመድ የነብዩ ሙሀመድ (ሰ.አ.ወ) ልጅ ናቸዉ ሲሉ መለሱ። ታድያ እኔም ከነዚህ ምርጥ የኢማን እና የተቅዋ ትምሳሌት የሆኑት እንቁ ሴቶቻችን ዉስጥ የመጀመርያዋን እና በአንሽየንት ግብፅ ዘመን የግብፅ ንግስት የነበረችዉን የአስያ መህዙም በነብዩ ሙሀመድ ኣንደበት ምርጥ የተባልችበትን እና በአላህ ቃል የኣማኞች ተምሳሌት የተባለችበትን ስራዋን ላስቃኛቹህ ወደድኩ።

አስያ ማንነች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አስያ መህዙም በግብፃዉያን አንደበት ነፈርታሪ ሜሪትሙት ትባል እንደነበር እና በዛን ሰአት የነበረዉ በቁርአን ላይ ፊርአዉን እየተባለ ከሰባ (70) ጊዘ በላይ በመጥፎነቱ የተጠቀሰዉ ሃያል ብሎም ጨካኝ የነበረዉ ንጉስ ራምሰስ ሁለተኛ ራምሰስ ሁለተኛ ተብሎ እንደሚጠራ ከግብፃዉያን የአንሽየንት ታሪክ ዉስት ይነበባል። አስያ ኢብን መህዙም በኣኢስላም ታሪክ ዉስጥ የተረገመዉ የፊርአዉን ሚስት በመባል ትታወቃለች ጠንካራ እና ተራ ያልነበረች አቋመ ፅኑ በመሆንዋ ዘመን ተሻግሮ ዘመን በመጣ ቁጥር የምእመናን ምሳሌ እየተባለች የመጨረሻዉ እና የኣልላህ ቃል በሆነዉ ቁራን ስትወሳ ኑራለች። ይህች ታላቅ ሴት በግብፃዉያን አንሽየንት ዘመን የንጉስ ዘር ነበረች። በዛን ስኣት ኣሉ ከሚባሉ ቆነጃጅቶች የምትመደበዉ ይህች ንግስት ጠንካራ እና ኣስተዋይ ሴት ነበረች። የንግስት ኣስያ ታሪክ የሚጀምረዉ ለኣቅማ ሀዋ ደርሳ ምድርን ከረገጡ ሃያላን ንጉስ ከሚባሉት ዉስጥ አንዱ የሆነዉን እና እኔ ነኝ ጌታ ብሎ በኣንዱ በብችኛዉ አላህ የካደዉን ንጉስ ኣግብታ ከቤቱ ከነገሰችበት ጊዜ ጀምሮ ነዉ።

وَقَالَ ٱلۡمَلَأُ مِن قَوۡمِ فِرۡعَوۡنَ أَتَذَرُ مُوسَىٰ وَقَوۡمَهُ ۥ لِيُفۡسِدُواْ فِى ٱلۡأَرۡضِ وَيَذَرَكَ وَءَالِهَتَكَ‌ۚ قَالَ سَنُقَتِّلُ أَبۡنَآءَهُمۡ وَنَسۡتَحۡىِۦ نِسَآءَهُمۡ وَإِنَّا فَوۡقَهُمۡ قَـٰهِرُونَ (١٢٧) surah al A'raf 127. ከፈርዖንም ሰዎች ታላላቆቹ (ለፈርዖን)፦ ሙሳንና ሰዎቹን በምድር ላይ እንዲያበላሹና ሙሳም አንተንና አማልክቶችህን እንዲተው ትተዋቸዋለህን? አሉ፤ ፦ወንዶች ልጆቻቸውን እንገድላለን፤ ሴቶቻቸውንም እናስቀራለን፤ እኛም ከበላያቸው ነን፤ አሸናፊዎች (ነን)፣ አለ። ሱረቱ አል-አዕራፍ 127. And the eminent among the people of Pharaoh said," Will you leave Moses and his people to cause corruption in the land and abandon you and your gods?" [Pharaoh] said, "We will kill their sons and keep their women alive; and indeed, we are subjugators over them." 7 surah al aeraf 127.

የፊራውን ትእዛዝ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ለፊርአዉን የኣንባገነንነት ማብቂያ ለህዝቦቹ ቀጥተኛ መንገድ መመርያ ለኣስያ ደግሞ በኣላህ ዘንድ መመረጫ የሆነዉ ይሄ የፊራዉን አዋጅ ከታወጀ ቡሃላ ብዙ የኢስራኤል ወንድ ህፃናት በኣንባ ገነኑ ፊርኣዉን ወታደሮች በግፍ ይረግፉ ጀመር። በዚህን ጊዜ የሙሳ (አሰ) እናት በኣንድ ጌታ የምታመን እስራኤላዊ ስለነበረች ጡት ያልጣለ ልጅዋን ሞት ፈርታ አላህን ከፊራዉን ወታደሮች እንዲጠብቅላት የተማፀነችዉ።

የሙሳ ከመሞት መዳን

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ወደ ሙሳም እናት «አጥቢው፣ በርሱም ላይ በፈራሽ ጊዜ በባሕሩ ውስጥ ጣይው አትፈሪም፣ አትዘኝም፣ እኛ ወዳንቺ መላሾቹና ከመልክተኞቹም አድራጊዎቹ ነንና» ማለትን አመለከትን፡፡ ( فَٱلۡتَقَطَهُ ۥۤ ءَالُ فِرۡعَوۡنَ لِيَڪُونَ لَهُمۡ عَدُوًّ۬ا وَحَزَنًا‌ۗ إِنَّ فِرۡعَوۡنَ وَهَـٰمَـٰنَ وَجُنُودَهُمَا ڪَانُواْ خَـٰطِـِٔينَ (٨) al qasas 7. And We inspired to the mother of Moses, "Suckle him; but when you fear for him, cast him into the river and do not fear and do not grieve. Indeed, We will return him to you and will make him [one] of the messengers." 28 አልቀሶስ number 7. የሙሳ (ኣ.ስ) እናት በኣላህ ላይ ኣንዳች ተስፋ ሳትቆርጥ እንደትእዛዙ የኣይንዋ ብሌን የሆነዉን ልጅዋን በባህር ላይ ኣንሳፈፈች በጌታዋ ተመክታ ጣለችዉ። የናይል ወንዝም ትከሻዉ ላይ ኣድርጎ የኣላህን ኣደራ ወደ ንግስት ኣስያ መዝናኛ ስፍራ ኣደረሰዉ። ይህንን ህፃን ያየች የኣስያ ኣገልጋይ ንግስትዋ እንድታይ ኣደረገች ንግስት ኣስያ እንዳየችዉ በሙሳ (ኣ.ስ) ፍቅር ወደቀች ከዝያም ለፊርአውን … ለእኔ የኣይኔ መርጊያ ነዉ ለኣንተም። ኣትግደሉት ሊጠቅመን ወይንም ልጅ ኣድርገን ልንይዘዉ ይከጀላል እና ኣለች። እነሱም ፍፃሜዉን የማያውቁ ሁነዉ ኣነሱት። ኣልቅሰስ 8-9.

فَٱلۡتَقَطَهُ ۥۤ ءَالُ فِرۡعَوۡنَ لِيَڪُونَ لَهُمۡ عَدُوًّ۬ا وَحَزَنًا‌ۗ إِنَّ فِرۡعَوۡنَ وَهَـٰمَـٰنَ وَجُنُودَهُمَا ڪَانُواْ خَـٰطِـِٔينَ (٨) وَقَالَتِ ٱمۡرَأَتُ فِرۡعَوۡنَ قُرَّتُ عَيۡنٍ۬ لِّى وَلَكَ‌ۖ لَا تَقۡتُلُوهُ عَسَىٰٓ أَن يَنفَعَنَآ أَوۡ نَتَّخِذَهُ ۥ وَلَدً۬ا وَهُمۡ لَا يَشۡعُر٩) 

አስያ ሙሳን ስታሳድገዉ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ኣስያ ሙሳን (ኣ.ስ) ልጅ ልታደርገዉ እስዋም እናት ልት ሆነዉ ኣነሳችዉ። ሙሳ (ኣ.ስ) በርሃብ ማልቀሱን ተያያዘዉ የሚመጡለትን ኣጥቢዎች ጡት ግን የኣንዳችዉንም ለመጥባት ፍቃደኛ ኣልነበረም። ለእኅቱም ተከታተይው አለቻት፡፡ እርሱንም እነሱ የማያውቁ ሲሆኑ በሩቅ ሆና አየችው፡፡ she said to his sister, "Follow him"; so she watched him from a distance while they perceived not. (ወደናቱ ከመመለሱ) በፊትም አጥቢዎችን (መጥባትን) በእርሱ ላይ እርም አደረግን፡፡ (እኅቱ) «ለእናንተ የሚያሳድጉላችሁን እነርሱም ለእርሱ ቅን አገልጋዮች የሆኑን ቤተሰቦች ላመልክታችሁን» አለችም፡፡ And We had prevented from him [all] wet nurses before, so she said, "Shall I direct you to a household that will be responsible for him for you while they are to him [for his upbringing] sincere?" እህቱ ስትከታተለዉ የሙሳን (ኣ.ስ) መራብ ኣይታ ነበር ወደ እናቱ የጠቆመቻቸዉ «ወደእናቱም ዓይንዋ እንድትረጋ፣ እንዳታዝንም፣ የአላህም የተስፋ ቃል እርግጥ መሆኑን እንድታውቅ መለስነው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ So We restored him to his mother that she might be content and not grieve and that she would know that the promise of Allah is true. But most of the people do not know. ኣልቅሰስ 11-13

وَحَرَّمۡنَا عَلَيۡهِ ٱلۡمَرَاضِعَ مِن قَبۡلُ فَقَالَتۡ هَلۡ أَدُلُّكُمۡ عَلَىٰٓ أَهۡلِ بَيۡتٍ۬ يَكۡفُلُونَهُ ۥ لَڪُمۡ وَهُمۡ لَهُ ۥ نَـٰصِحُونَ (١٢) فَرَدَدۡنَـٰهُ إِلَىٰٓ أُمِّهِۦ كَىۡ تَقَرَّ عَيۡنُهَا وَلَا تَحۡزَنَ وَلِتَعۡلَمَ أَنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقٌّ۬ وَلَـٰكِنَّ أَڪۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ (١٣)

የአስያ መስለም

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሙሳ (ኣ.ስ) በእናቱ ጡት በኣሳዳጊዉ ንግስት ኣስያ ተንከባክቦ ከሙሉ ቤተሰቡ ጋር በፊርኣዉን ቤተመንግስት ዉስጥ የሚጠላ ዘር ግና የሚወደድ ህፃን ሁኖ ኣደገ። ከለታት ኣንድ ቀን ጨለማ በብርሃን እንደሚገፈፈዉ ሁሉ ሙሳም (ኣ.ስ) የፊራዉንን በዳይነት ሊገፍ ነብይ ሆነ። ከዛም ህዝቦቹን እና የፊርኣዉን ቤተመንግስት ዉስጥ ያሉ ሰዎችን እኔ ከኣንዱ ከእዉነተኛዉ ጌታየ እና ጌታቹህ የተላኩ የኣላህ መልእክተኛ ነኝ ፊርኣዉንም እንደኛዉ ሰዉ እንጅ ፈጣሪ ኣይደለም እነኣሙንም ሆኑ ሌሎች ጣኦታትም የማይሰሙ የማይፈጥሩ ገኡዛን እንጅ ሌላ ኣይደሉም ብሎ በህፃንነቱ ያሳደገዉን አባቱን የኣላህን ጠላት ጠላቱ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ አስያም በሙሳ መንገድ ቆመች እስዋም ባልዋን ጠላት እደረገች። በሱ ላይ የካደበትን ሁሉ ኣይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣ እያወቀች ብሎም ቤተሰብዋን ክብርዋን እና ዝናዋን ብሎም ሂወትዋን እንደሚያሳጣት እያወቀች በቤተ መንግስቱ ሁና ሌላን እዉነተኛዉን እላህን ማገልገልዋን ቀጠለች። ከዱንያ እና በዉስጡ ካሉ ጥቅሞች ይልቅ የኣላህን ቃል ትእዛዙን ኣስበለጠች።ለጌታዋ ኑራ ለጌታዋ መሞትን መረጠች።

ከእለታት ኣንድ ቀን ሙሳ (ኣ.ስ) ከፊራዉን እውቅ ድግምተኞች እና ኣስማተኞች ጋር የኣላህን ተኣምር ለማሳየት ተወዳድሮ አሽነፈ ከዛም ቡሃላ ጠንቋዮችን ጨምሮ ብዙ ህዝቦች በሙሳ ጌታ አምነናል ሲሉ ኣመኑ በፊርኣዉን እና በኣሙን ጌትነት ላይ ካዱ።

አይደለም ጣሉ፣ አላቸው፤ ወዲያውም ገመዶቻቸውና ዘንጎቻቸው ከድግምታቸው የተነሳ እነርሱ የሚሮጡ (እባቦች) ሆነው ወደርሱ ተመለሱ። He said, "Rather, you throw." And suddenly their ropes and staffs seemed to him from their magic that they were moving [like snakes]. ሙሳም በነፍሱ ውስጥ ፍርሃት አሳደረ. And he sensed within himself apprehension, did Moses. አትፍራ አንተ የበላዩ አንተ ነህና አልነው። Allah said, "Fear not. Indeed, it is you who are superior. አትፍራ አንተ የበላዩ አንተ ነህና አልነው። Allah said, "Fear not. Indeed, it is you who are superior. ድግምተኞቹም ሰጋጆች ሁነው ወደቁ፤ በሃሩንና በሙሳ ጌታ አመንን አሉ። So the magicians fell down in prostration. They said, "We have believed in the Lord of Aaron and Moses." surah ሱረቱ ጣሀ (66-70) (٦٦) فَأَوۡجَسَ فِى نَفۡسِهِۦ خِيفَةً۬ مُّوسَىٰ (٦٧) قُلۡنَا لَا تَخَفۡ إِنَّكَ أَنتَ ٱلۡأَعۡلَىٰ (٦٨) وَأَلۡقِ مَا فِى يَمِينِكَ تَلۡقَفۡ مَا صَنَعُوٓاْ‌ۖ إِنَّمَا صَنَعُواْ كَيۡدُ سَـٰحِرٍ۬‌ۖ وَلَا يُفۡلِحُ ٱلسَّاحِرُ حَيۡثُ أَتَىٰ (٦٩) فَأُلۡقِىَ ٱلسَّحَرَةُ سُجَّدً۬ا قَالُوٓاْ ءَامَنَّا بِرَبِّ هَـٰرُونَ وَمُوسَىٰ ((٧ surah taha 66-70.

የተአምሩ ዉጤት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ይህ ከሆነ ከቀናቶች ቡሃላ በሃጅ ወቅት እንደሚሰዋ በግ ከሌላዉ ጊዜ የበለጠ ቁጥራቸዉ የበዛ አማኝ ህዝቦች መታረዳቸዉን ቀጠሉ። ከነዛ ዉስጥ የፊርአዉን ልጅ ፀጉር አበጣሪ የነበረችዉ አማኝ የምታበጥርበት ማበጠርያ ከእጅዋ ሲወድቅባት በድንጋጤ የኣላህን ስም በመጥራትዋ እማኝነትዋ ታወቀባት በሙሳ ጌታ እንድትክድ በልጆችዋ ስቃይ ስትቀጣ ከጡትዋ ያልወረደዉ ህፃንም ልክ አንደሌሎች ወንድሞቹ መቀጫ ሊሆን ሲል በድንጋጤ እና በፍርሃት ዉስጥ ሁና ስታለቅስ ያያትን እናቱን የኣላህን ስም ጠርቶ አፉን እየፈታ ታገሽ በኣላህ ላይ ተስፋ ኣድርጊ የሚል ኣስገራሚ የህፃን አንደበት ሰምታ ከጡትዋ ነጥቀዉ የፈላ ዘይት እራት ካደረጉት ቡሃላ እና በልጆችዋ ሂወት ሳትሳሳት ለነብስዋም ሳትሳሳ በጌታዋ ኣንድነት እንዳመነች ከነልጆችዋ ከተጠበሰችዋ ምስኪን እናት ሞት ቡሃላ።

የአስያ እምነትዋን ግልጽ ማዉጣት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አስያ ያለችበትን የእምነት የመዳን ብርሃን ደብቃ መኖር ኣልቻለችም የእምነት ወንድም እህቶችዋ ሞት ይበልጥ ፊርአዉንን እንድትጠላዉ እና እንድትንቀዉ ኣደረጋት። እናም እንደሌሎቹ ሽሂድ ልትሆን ላመነችበት ጌታዋ ልትሞት ወሰነች። አማኝነትዋንም ለጨካኙ ፊርአዉን ገለፀች እራስዋን ለእሳት ኣሳልፋ ሰጠች ልትሞት ወሰነች። አማኝነትዋንም ለጨካኙ ፊር አዉን ገለፀች እራስዋን ኣሳልፋ ሰጠች። ፊርአዉን የዉቦች ዉብ የሆነችዉን ዉድ ሚስቱን ከመቅጣቱ ነብስዋን ላትመለስ ከመሸኘቱ በፊት በሙሳ (ኣ.ስ) ጌታ ትካድ በሚል እናትዋን ሽምግልና ላከ። አስያ ግን በሃቅ መንገድዋ ላይ ቤተሰብዋን ንግስናዋን እና በኣለም ላይ ሃያል ተብሎ የሚጠራዉን ንጉስ ማስገባት ኣልፈለገችም። እነዚህን እና አላህን ማመዛዘን ማለት ወርቅ በኣፈር የመቀየር ያህል ሆነባት። በፍፁም ኣልስማማም በጌታዋ ላይ ያላትን ፅናት አወጀች። ፊርኣዉን በኣስያ ተስፋ ስለቆረጠ ሊገላት እንደሌሎች አማኞች ሸሂድ ልያደርጋት ወሰነ። በዚህን ጊዘ ለጌታዋ እንዲህ ስትል እጅዋን ኣነሳች:: ለነዚያ ለአመኑትም የፈርዖንን ሴት አላህ ምስል አደረገ፤ ጌታዬ ሆይ! አንተ ዘንድ በገነት ውስጥ ለኔ ቤትን ግንባልኝ፤ ከፈርዖንና ከሥራውም አድነኝ፤ ከበደለኞቹ ሕዝቦች አድነኝ ባለች ጊዜ። አል- ተሕሪም 1) وَضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلاً۬ لِّلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱمۡرَأَتَ فِرۡعَوۡنَ إِذۡ قَالَتۡ رَبِّ ٱبۡنِ لِى عِندَكَ بَيۡتً۬ا فِى ٱلۡجَنَّةِ وَنَجِّنِى مِن فِرۡعَوۡنَ وَعَمَلِهِۦ وَنَجِّنِى مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّـٰلِمِينَ (١١) And Allah presents an example of those who believed: the wife of Pharaoh, when she said, "My Lord, build for me near You a house in Paradise and save me from Pharaoh and his deeds and save me from the wrongdoing people." at tehrim 11

አስያ ለጌታዋ የጠየቀችዉ ጥያቄ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አስያ በምድር ላይ ያሉ ነገሮችን ሳይሆን በጀነት የኣላህን ጉርብትና ነበር ጌታዋን የተማፀነች ድሎትን ሳይሆን በተውሂድ መሞትን እንዲሁም በምድር ላይ ካሉ የኣላህ ጠላቶች እንዳትሆን ነበር ዱኣዋ። ይህንን ካለች ብሃላ የግብፅ የኣን ሽየንት ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከክርስቶስ ዘመን በፊት ወይንም በ1179 B.C.E (before christian era) ከዚህ ኣለም ተሰናበተች ወደኣንዱ እና ብቸኛ ጌታዋ ጉርብትና ወደጀነት ኣቀናች።

ጥያቄ ከአንባቢዎች አንዱ

  • ️⃣ለምን የተወለደችበት ቀን አል አልታወቀም???
  • ️⃣መሃመድ የመጣው ከክርስቶስ በኋላ በ6 ዓም ነበረ።ማን ያርዳ የቀበረ ማን ይናገር የነበረ ነውና"መቼ ነሮበት በቼ አይቶት ነው ይህን የተናገረው???