ማይጨው
ማይጨው | |
ማይጨው (ትግርኛ ) በስሜን ኢትዮጵያ ያለች ታሪካዊ ከተማ ናት። ከአዲስ አበባ 665 ኪሎ ሜትር ወደ ስሜን በአዲስ አበባ-መቐለ መንገድ በትግራይ ክልል ደቡባዊ ክፍል ስትገኝ ኬክሮሷና ኬንትሮሷ 12°47′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°32′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ከፍታዋም 2,479 ሜትር ነው።
በ1997 ዓ.ም. ከማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በቀረበው ቁጥር መሠረት የማይጨው ጠቅላላ ሕዝብ ቁጥር 34,379 ሰዎች እንደ ነበር ይገመታል። ከነዚህም 16,702 ወንዶችና 17,222 ሴቶች ነበሩ። በ1984 ብሄራዊ ቆጠራ ግን 19,757 ኗሪዎች ነበሩ።
በማይጨው አካባቢ ግጥሚያ በመጋቢት 22 ቀን 1928 ዓ.ም. በጣልያን ጦርነት ጊዜ የፋሺስት ሃያላት በመሳርያዎች ምክንያት ድል አድርገው ወደ አዲስ አበባ ቀረቡ። በጦርነቱም የተሰውት አርበኞች አባቶች አፅም በከተማዋ ደቡባዊ ክፍል በሚገኘው ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን በተዘጋጀላቸው ቦታ በክብር አርፎ ይገኛል፡፡
በተጨማሪም መሬት ለኣራሹ (የኢትየጵያ ተማሪዎች አመፅ) መሪ እና የወቅቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ የተማሪዎች ፕሬዚደንት የነበረው በዘውዳዊ ስርዓት ታጣቂዎች የተገደለው ጥላሁን ይግዛው መቃብር በከተማዋ በሚገኘው ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን (ማርያም ሕዝባ) ላይ ይገኛል፡፡
በከተማዋ ካሉት የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል ራያ ዩኒቨርሲቲ፣ አንጋፋው ማይጨው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፣ ጥላሁን ግዛው ቴክኒክ ኮሌጅ እና ማይጨው እርሻ ኮሌጅ ይጠቀሳሉ፡፡ ራያ ቢራ ፋብሪካ እና ማይጨው ፓርቲክል ቦርድ (ችፑድ ፋብሪካ) በከተማዋ ይገኛሉ፡፡
በአጠቃላይ ከተማዋ በኢትዮጵያ ካሉ ለኑሮ አመቺ ከሆኑሞ ም ር ጥ አካባቢዎች መካከል ትጠቀሳለች፡፡
የሃይለ ሓጎስ እና የሓማሴን ሓድገምበስ የትውልድ አገር ነች
|