[go: up one dir, main page]

Jump to content

መሪካሬ

ከውክፔዲያ

መሪካሬ (ወይም መሪካራ) በመጀመርያው ጨለማ ዘመን (10ኛው ሥርወ መንግሥት) በግብጽ (ከሄራክሌውፖሊስ) የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ትምህርት ለመሪካሬ የተባለው ግብጽኛ ጽሑፍ ለእርሱ እንደ ተጻፈ ይታመናል። ይህ ጽሑፍ ከአባቱና ከቀዳሚዎቹ የተወረሰው የአገዛዝ ምክር አለበት። አባቱ በደቡብ ጢኒስን እንደማረከው ይገልጻል፣ ልጁ መሪካሬ ደቡብ ግብጽን በትዕግሥት እንዲገዛው ይመክረዋል።

ሆኖም ከደቡብ ጋር የነበረው ችግር አልቀረም ነበር። እርሱ በስሜን በሄራክሌውፖሊስ እየገዛ በ2121 ዓክልበ. ግድም ተወዳዳሪው 11ኛው ሥርወ መንግሥት (በማኔጦን አቆጣጠር) በጤቤስ በደቡብ ግብጽ በመንቱሆተፕ ነብኸፐትሬ ሥር ተነሣ። በመንቱሆተፕ 14ኛው ዓመት፣ መሪካሬ በስሜን ሆኖ ከመንቱሆተፕ ጋራ ጦርነት ያደርግ ነበር። በዚህ ጦርነት የአሥዩት ገዦች ተፊቢ እና ልጁ ቀቲ ለመሪካሬ ታማኝ ሆነው በጤቤስ ግዛት ላይ እንደ ዘመቱ ይታወቃል።

በ2081 ዓክልበ. ግድም መሪካሬ ሞተና የ10ኛው ሥረ መንግሥት መጨረሻ ፈርዖን እንደ ነበር ይመስላል። ሄራክሌውፖሊስ ያንጊዜ ለመንቱሆተፕ በመውደቁ ግብጽ እንደገና ተዋሀደ።

  • Wolfgang Kosack: Berliner Hefte zur ägyptischen Literatur 1 - 12: Teil I. 1 - 6/ Teil II. 7 - 12 (2 Bände). Paralleltexte in Hieroglyphen mit Einführungen und Übersetzung. Heft 8: Die Lehre für König Merikarê. Verlag Christoph Brunner, Basel 2015. ISBN 978-3-906206-11-0.
ቀዳሚው
ሰነን-...?
ግብፅ ፈርዖን ተከታይ
2 መንቱሆተፕ
(ከ2121 ዓክልበ. ግድም)