1966
1966 አመተ ምኅረት
- መስከረም 10 ቀን - ቢሊ ጂን ኪንግ፣ ሴት ቴኒስ ተጫዋች፣ ቦቢ ርግስን በሂውስተን በማሸንፍ «የጾታዎች ቴኒስ ውድድር» አሸናፊ ሆነች።
- መስከረም 14 ቀን - ጊኔ-ቢሳው ነጻነቱን ከፖርቱጋል አዋጀ።
- መስከረም 26 ቀን - የዮም ኪፑር ጦርነት በእስራኤልና በግብፅ፣ ሶርያና ሌሎች አገራት መካከል ተጀመረ።
- መስከረም 30 ቀን - የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ስፒሮ አግንው ማዕረጉን ተወ።
- ጥቅምት 2 ቀን - ጄራልድ ፎርድ አዲሱ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነ።
- ጥቅምት 13 ቀን - እስራኤል የትኩስ ማቆም ስምምነት ሰብረው ወደ ካይሮ ስለ ቀረቡ፣ አጼ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የእስራኤልና የኢትዮጵያ ግንኙነቶች ለማቋረጥ ፈቀዱ። በዚሁም ቀን በዋተርጌት ቅሌት ምክንያት የአሜሪካ ምክር ቤት የመክሰስ ፍርድ በፕሬዚዳንት ሪቻርድ ኒክሰን ላይ ለመከራከር ጀመረ።
- ጥቅምት 15 ቀን - በሁለተኛ ስምምነት የ አረብ-እስራኤል ጦርነት በይፋ ተጨረሰ። እስራኤል ተጨማሪ መሬት በግብጽና በሶርያ ለጊዜው ይዟል።
- ኅዳር 8 ቀን - ኒክሰን ስለ ዋተርጌት ቅሌት ሲጠቀስ «እኔ ወንጀለኛ አይደለሁም» ይላል።
- ጥር 28 ቀን - በካሊፎርኒያ የራንዶልፍ ሄርስት ልጅ ልጅና ወራሽ ፓቲ ሄርስት «ሲምቢዮኒዝ አርነት ሥራዊት» በተባለ ሽብርተኛ ቡድን ተጠለፈች፤ በኋላም የቡድን አባል ለመሆን ቈረጠች።
- የካቲት 7 ቀን - በአዲስ አበባ የዩኒቬርሲቲ ተማሮች አድማ ጠሩ።
- የካቲት 13 ቀን - የአሜሪካ ታዋቂና የቴሌቪዥን ትርኢት የነበራቸው ዘፋኝ ባለቤቶች ሶኒ እና ሼር ቡደን አባል የነበረችው ሼር የትዳር ፍች መፈልግዋን አሳወቀች።
- የካቲት 21 ቀን - የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድ ማዕረጋቸውን ተዉ።
- ሚያዝያ 19 ቀን - አንዳንድ የኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች በሥራዊት ታሠሩ።
- ሐምሌ 13 ቀን - የቱርክ ሥራዊት ወደ ስሜን ቆጵሮስ ወረሩ።
- ሐምሌ 15 ቀን - የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው መኮንን ማዕረጋቸውን ተዉ።
- ሐምሌ 22 ቀን - አሜሪካዊት ዘፋኝ ካሥ ኤሊየት በ32 አመት በአደጋ አረፈች።
- ነሐሴ 3 ቀን - ሪቻርድ ኒክሰን ማዕረጉን ተዉና በሱ ፈንታ ጄራልድ ፎርድ አዲስ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆኑ።
- ጳጉሜ 3 ቀን - ፕሬዚዳንት ፎርድ ለቀዳሚው ኒክሰን ሙሉ ይቅርታ ሰጠው። በአይዳሆ የሞቶር ቢስክሌት ድፍረተኛ ኢቨል ክኒቨል ገደል ለመዝለል ሙከራ አልተከናወነም።
- ጳጉሜ 5 ቀን - ጊኔ-ቢሳው ነጻነቱን ከፖርቱጋል አገኘ።
ክፍለ ዘመናት፦ | 19ኛ ምዕተ ዓመት - 20ኛ ምዕተ ዓመት - 21ኛ ምዕተ ዓመት |
አሥርታት፦ | 1930ዎቹ 1940ዎቹ 1950ዎቹ - 1960ዎቹ - 1970ዎቹ 1980ዎቹ 1990ዎቹ
|
ዓመታት፦ | 1963 1964 1965 - 1966 - 1967 1968 1969 |
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |