ጥር ፲፭
Appearance
(ከጥር 15 የተዛወረ)
ጥር ፲፭ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፴፭ ኛው ዕለት ሲሆን ፳ ኛው የበጋ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፪፻፴፩ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፪፻፴ ዕለታት ይቀራሉ።
- ፲፭፻፵፬ ዓ/ም - በታሪክ ዘገባ በብዛት የሰው ነፍስ የጠፋበት ታላቁ የ'ሻንግዚ' የመሬት እንቅጥቅጥ በቻይና ሲከሰት እስከ ስምንት መቶ ሠላሳ ሺህ ሰዎች እንደሞቱ ይገመታል።
- ፲፱፻፵፰ ዓ/ም - በብሪታኒያ የኢትዮጵያ ስምንተኛው አምባሳዶር አቶ አማኑኤል አብርሐም የሹመት ደብዳቤያቸውንና የአቶ አበበ ረታን የሽረት ደብዳቤ ለዳግማዊት ንግሥት ኤልሣቤጥ በባኪንግሃም ቤተ መንግሥት ቀርበው አስረከቡ። [1]
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - የአዋሽ ፩ኛ እና ፪ኛ ግድቦች የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጫ ሥነ ሥርዓት ላይ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መርቀው መሠረቱን ተከሉ።
- ፲፱፻፹፩ ዓ/ም - በቀድሞው የሶቪዬት ሕብረት ክልል ፤ በአሁኑ ታጂኪስታን ውስጥ የተከሰተ የመሬት እንቅጥቅጥ ፪፸፬ ሰዎች ገደለ።
- ፲፱፻፺፱ ዓ/ም "ንጉሠ ነገሥቱ - የፈላጭ-ቆራጭ መሪ አወዳደቅ" (The Emperor: Downfall of an Autocrat)በሚል አርዕስት ስለ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አወዳደቅ የጻፈው የፖሎኝ ተወላጅ፣ ጋዜጠኛና ደራሲ ሪስዛርድ ካፑቺንስኪ (Ryszard Kapuscinski)አረፈ።
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/January_23
- (እንግሊዝኛ) P.R.O, FO 371/190144
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |