ሰኔ ፲፮
Appearance
(ከሰኔ 16 የተዛወረ)
ሰኔ ፲፮ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፹፮ኛው ቀን ሲሆን የፀደይ (በልግ)ወቅት ፹፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፹ ቀናት፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፸፱ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የሱዳን ፕሬዚደንት ጃፋር አል ኒሜሪ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትን ሊቀ መንበር የናይጄሪያውን ፕሬዚደንት ጄኔራል ያኩቡ ጋዋንን በመወከል በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መኻል ስለተነሳው ግጭት ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር የሁለት ቀን ውይይት ለማድረግ አዲስ አበባ ገቡ።
- ፲፱፻፸፯ ዓ/ም ሕንዳዊ የሲክ አመጸኛ ቡድን ከሞንትሪያል ተነስቶ በሎንዶን በኩል ወደ ዴልሂ በረራ ላይ የነበረውን የሕንድ አየር መንገድ፣ በረራ ቁጥር ፻፹፩ ጥያራ በድብቅ በጫኑት ቦምብ ፍንዳታ አየርላንድ አጠገብ ባህር ውስጥ ሲሰምጥ ሦስት መቶ ሃያ ዘጠኙም የቦይንግ ፯፻፵፯ቱ (B747) ተሣፋሪዎች ሞተዋል።
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1660 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1973
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |