ሴኬም
Appearance
ሴኬም (ዕብራይስጥ፦ שְׁכֶם /ሽኬም/) በከነዓን እና በኋላ በእስራኤል የነበረ ከተማ ነው።
- 2110 ዓክልበ. - አብርሃም በሴኬም ሲያልፍ መስዊያ ለእግዚአብሔር ይሠዋል (ዘፍ. ፲፪)።
- 2100 ዓክልበ. አካባቢ - በኤብላ የኤብላ ጽላቶች የሴኬም ጣኦት «ራሳፕ» ነው ይላሉ። (የኤብላ ጽላቶች)
- 1928 ዓክልበ. - የያዕቆብ (እስራኤል) ቤተሠብ ስለ እኅታቸው ስለ ዲና የሴኬም ባላባት ኤዊያዊው ኤሞርን አሸነፈ፤ ሴኬም ሠፈር አጠፋ። (ዘፍ. ፴፬)
- 1884 ዓክልበ. - የግብጽ ፈርዖን 3 ሰኑስረት በ«መንቱ» (ምድያም)ና በረጨኑ (ከነዓን) ላይ ዘምቶ፣ በ«ሰክመም» (ሴኬም) አሸነፋቸው። (የሰበክ-ሁ ጽላት)
- 1587 ዓክልበ. - ኢያሱ ወልደ ነዌ በሴኬም ተቀበረ። (ኢያሱ ፳፬)
- 1360 ዓክልበ. አካባቢ - «ሻክሙ» (ሴኬም) የንጉሥ ላባያ መቀመጫ፣ እርሱ ወታደሮች ከሃቢሩ ወገን ይቀጥራል። (አማርና ደብዳቤዎች)
- 1252 ዓክልበ. - ጌዴዎን አርፎ ልጁ ከሴኬማዊት ቁባት ጋር፣ አቢሜሌክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ ሴኬም አመጸበትና ከተማውን አጠፋ። (መሳፍንት ፱)
- 936 ዓክልበ. - በሰሎሞን መሞት ሴኬም እስከ 915 ዓክልበ. ድረስ የስሜን መንግሥት የእስራኤል መንግሥት መቀመጫ ሆነ። (፩ ነገሥታት)
- 595 ዓክልበ. - ሴኬም የሳምራውያን ቅዱስ ቦታ ሆነ። (ፍላቪዩስ ዮሴፉስ)
- 136 ዓክልበ. - ከመቃብያን ወገን ዮሐንስ ሂርቃኖስ የሳምራውያን ቤተ መቅደስ በሴኬም አጠፋ። (ዮሴፉስ)
- 2 ዓክልበ. - ሴኬም ወደ ሮሜ መንግሥት ሶርያ ጠቅላይ ግዛት ተጨመረ።
- 25 ዓ.ም. ግድም - ኢየሱስ በ«ሲካር» (ሴኬም) ሲያልፍ መሲህ መሆኑን ለሳምራዊት ይገልጻል። (ዮሕ ፬፡፳፮)
- 59 ዓ.ም. - ገሊላ በሮማውያን ላይ ሲያመጽ ሴኬም በኬሬያሊስ እጅ ይጠፋል።
- 64 ዓ.ም. - የሮሜ ቄሣር ቤስጳስያን «ኔያፖሊስ» («አዲስ ከተማ») በሴኬም ሥፍራ አጠገብ አሠራ። ይህ ዛሬ ናብሉስ ይባላል።