[go: up one dir, main page]

Jump to content

ራያ

ከውክፔዲያ
The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.

፭ራያ በደቡብ ትግራይ እና በሰሜን ወሎ የሚገኝ ህዝብ እና አካባቢ ነው። ይህ ህዝብ በትግራይ እና በወሎ ካሉ ደማቅ ባህሎች ባለ ቤት ስርዓት እና ወግ፡ ማለትም እንደ አነጋገር፡ አለባበስ፡ የሰርግ ፡ የለቅሶ ስነስርዐት ያለው ኩሩ እና ጀግና ህዝብ ነው። የራያ ህዝብ ከሚደነቅበትና ከሚያስደስት ባህሉ ሁሉም የእምነት ተከታዮች በተለይም ሙስሊም ክርስቲያን ሳይል በመቻቻል በህብረት በአንድ ላይ ተከባበሮ የሚኖር ህዝብ ሲሆን የአለባበስ ባህሉ ሌላው የሚደነቅለት አና ባህላዊ ጭፈራው ሲያዩት የሚያስግርም አና የሚያስድስት ነው። ከባህላዊ ጭፈራዎቹ እንደ "ጉማየ" "መጋልዋ" ፡ ወዘተ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ህዝቡ የሚኖርበት አከባቢ እንደሚከተለው ይዋሰናል። በሰሜን ወጀራትና እንደርታ፣ በደቡብ የጁ (ጉባ ላፍቶ) እና ሃብሩ፣ በምስራቅ ዓፋር፣ በምዕራብ ደግሞ ግዳን እና ዋግኽምራ ያዋሱኑታል።